ኢትዮጵያ በሰው መነገድ ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መሠረተች
የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሊቢያ የሚደርስ የወንጀል ሰንሰለት በመዘርጋት በ3,887 ተጎጂዎች ላይ በሰው መነገድ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።
ተከሳሾቹ ዜጎችን ወደ አውሮፓ እናሻግራለን በማለት በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ በማጓጓዝ፤ በበረሃ መጋዘኖች ውስጥ በማገትና በማሰቃየት ገንዘብ ሲቀበሉ ቆየተዋል ተብሏል።
በድርጊቱ ምክንያት የ133 ተጎጂዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን 76 ሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል ተብሏል።
ተከሳሾቹ የተጎጂዎችን ስቃይ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቤተሰቦች በመላክ፤ ከ2015 እስከ 2018 ዓ.ም ታኅሳስ ድረስ ብቻ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ መቀበላቸው በክሱ ተብራርቷል።
በቡድን መሪው ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) እና ሌሎች ተከሳሾች ላይ ከባድ በሰው መነገድ፣ በወንጀል የተገኘን ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ያለፈቃድ የባንክ ሥራ መሥራት የሚሉ 16 ክሶች ቀርበውባቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X