አውሮፓ ዩክሬንን በጦር መሣሪያ ለማስታጠቅ ድሮኖችን በስፋት የማምረት እንቃስቃሴ ጀምራለች - የሩሲያ ሚኒስቴር

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.04.2026
ሰብስክራይብ
አውሮፓ ዩክሬንን በጦር መሣሪያ ለማስታጠቅ ድሮኖችን በስፋት የማምረት እንቃስቃሴ ጀምራለች - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

በርካታ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት፤ የዩክሬን ጦር እያጋጠመው ያለውን ከፍተኛ ኪሳራ እና የሰው ኃይል እጥረት ለመሙላት የድሮን ምርት እና አቅርቦትን ለመጨመር ባለፈው መጋቢት 17 ውሳኔ ማሳለፋቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።

ይህ እርምጃ የአውሮፓ አኅጉር ወታደራዊ-ፖለቲካዊ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲባባስ የታሰበ እና የአውሮፓ ሀገራትን በተግባር የዩክሬን "ስትራቴጂካዊ የኋላ ደጀን" እያደረጋቸው ነው ሲል አጽንኦት ሰጥቷል።

"በአውሮፓ የተሠሩ ድሮኖች ሩሲያ ላይ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም ጥቅም ላይ ከዋሉ የማይገመት መዘዞችን ያስከትላሉ" ሲል ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል።

የአውሮፓ መሪዎች ተግባር የአኅጉሪቱን ደህንነት ከማጠናከር ይልቅ ሀገራቸውን ከሩሲያ ጋር ወደሚደረግ ጦርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሳባቸው ይገኛል።

የመከላከያ ሚኒስቴሩ በተጨማሪም በመላው አውሮፓ የሚገኙ የዩክሬን እና የጋራ የድሮን ማምረቻ ተቋማትን እንዲሁም የመለዋወጫ አምራቾችን አድራሻ የያዘ ዝርዝር ይፋ አድርጓል። ማምረቻዎቹ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ላትቪያ፣ ሊቱዌኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ቱርክ እና እስራኤል ውስጥ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0