ኢትዮጵያ የሴቶችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ አርአያ ሀገር ናት - ኮሜሳ
የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ ጥምረት (ኮሜሳ) የኢትዮጵያ የሴቶች ተጠቃሚነትና የጾታ እኩልነትን የማረጋገጥ ጥረት ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ መሆኑን ገልጿል።
ይህ የተባለው በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ በተካሄደው 15ኛው የኮሜሳ የሴቶችና የጾታ እኩልነት ቴክኒካዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
በጉባኤው ኢትዮጵያ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ ውጤታማ እርምጃዎችን እየወሰደች እንደሆነ ተመላክቷል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሒክማ ኬይሬዲን “እንደሀገር በተሠሩ ሥራዎች የሴቶችን እኩልነት በሁሉም ማዕቀፍ ውስጥ ለማምጣት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ውሳኔ ሰጪነት ላይ ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ የማታወቀው በጣም ብዙ መሠረታዊ ለውጦች መጥተዋል” ሲሉ ለኮሜሳ ሴክሬታሪያት በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡
ጉባኤው በድርጅቱ የጾታ ፖሊሲ አፈጻጸም ዙሪያ የልምድ ልውውጥ የተካሄደበት እንደነበር የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ተንቀሳቃሽ ምሥሉ ከኮሜሳ ሴክሬታሪያት የማኅበራዊ ገጽ የተገኘ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X