የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ 76 በመቶ መድረሱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ 76 በመቶ መድረሱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀደም ሲል በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተሠማራው ዊቢይውልድ ኩባንያ፤ ሲጠናቀቅ 6,460 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም የሚኖረውን ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተረክቦ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስለግድቡ ቁልፍ መረጃዎች፦

🟠 ግድቡ ሲጠናቀቅ 201 ሜትር ቁመትና 1 ሺህ 12 ሜትር ርዝመት ይኖረዋል፣
🟠 6.8 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ይይዛል፣
🟠 አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 2.5 ቢሊየን ዩሮ ይፈጃል፣
🟠 ፕሮጀክቱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ኮይሻ ወረዳ እየተገነባ ይገኛል፡፡


የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፤ ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን የማሟላት ሥራ በቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።


ተንቀሳቃሽ ምሥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግድቡን ግንባታ ሲጎበኙ ያሳያል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0