ዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያን ምርቶች ለዓለም አቀፉ ገበያ የበለጠ ተደራሽ ያደርጋል - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ዋይልድቤሪስ
ዋይልድቤሪስ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.04.2026
ሰብስክራይብ
ዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያን ምርቶች ለዓለም አቀፉ ገበያ የበለጠ ተደራሽ ያደርጋል - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

የሩሲያ የኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረክ ዋይልድቤሪስ፤ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን ወደ ሩሲያ ገበያ በቀላሉ ለማድረስ እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር፤ የኩባንያውን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀል አስመልክቶ ለንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ ለመንግሥት ተወካዮች እና ለተለያዩ አካላት በተዘጋጀ የማስተዋወቂያ መርኃ-ግብር ላይ ተገልጿል።


የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታ ይድነቃቸው ወርቁ፤ የዋይልድቤሪስ ወደ ኢትዮጵያ መግባት “በሁለቱ ሀገራት መካከል የወጪ እና ገቢ ንግድ ምጥጥን ለማረጋገጥ እንዲሁም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የበለጠ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማስቻል ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር” ገልጸዋል።


የኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረኩ በ2025 ከ73.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግብይት እንደተካሄደበት የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ገልጸዋል። በወር 81 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች እንደሚጎበኙት እና በቀን 25 ሚሊዮን ትዕዛዞችን እንደሚያስተናግድም አስታውቀዋል።

ዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያን ምርቶች ሩሲያ ውስጥ መሸጥ እንደጀመረ የመገበያያ መድረኩ መስራች ታቲያና ኪም ቀደም ሲል አስታወቀዋል፡፡ መገበያያው በቀጣይ ምዕራፍ ለኢትዮጵያውያን ሸማቾች ክፍት ይሆናልም ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0