ሞስኮ እና ቤጂንግ የደቡባዊውን ዓለም አንድነት ለመጠበቅ ሕጋዊ ጥቅሞቻቸውን ማስከበር አለባቸው - ሺ ጂንፒንግ

ሞስኮ እና ቤጂንግ
ሞስኮ እና ቤጂንግ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.04.2026
ሰብስክራይብ
ሞስኮ እና ቤጂንግ የደቡባዊውን ዓለም አንድነት ለመጠበቅ ሕጋዊ ጥቅሞቻቸውን ማስከበር አለባቸው - ሺ ጂንፒንግ

የቻይና ፕሬዚዳንት ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ዓለም ላይ በክፍለ ዘመኑ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥ በተጋረጠበት በዚህ ወቅት ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት እያጠናከረች እንደሆነ ገልፀዋል።

ሁለቱ ሀገራት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ሥልጣን እና ዘላቂነት ወደ ነበረበት ለመመለስ በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ሺ ጂንፒንግ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህም በሻንጋይ የትብብር ድርጅት እና በብሪክስ ውስጥ የሚከናወኑ የጋራ ሥራዎችን በማስቀጠል መከናወን እንዳለበት አመልክተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0