ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በመተባበር ሳተላይቶችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም እንደምትፈልግ አስታወቀች

ኢትዮጵያ፣ ሩሲያ
ኢትዮጵያ፣ ሩሲያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በመተባበር ሳተላይቶችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም እንደምትፈልግ አስታወቀች

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ከሩሲያ የጠፈር ተቋም (ሮስኮስሞስ) ጋር የሳተላይት መገጣጠሚያ እና ሙከራ ማዕከል በኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት በቶሎ እንዲደረግ ጠይቀዋል።


"እኛ ሳተላይቶች ሲመጥቁ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ምድር ተገንበተው ሙከራ ሲደረግና ሲመጥቁ ጭምር ማየት እንፈልጋለን” ሲሉ በዩሪ ጋጋሪን የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት ላይ መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።


"እንሂድ!" የሚለውን የዩሪ ጋጋሪንን ቃል በተምሳሌትነት ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ስምምነቱን ዳር ለማድረስ አስቸኳይ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ በማቅረብ፤ ማዕከሉ የምስራቅ አፍሪካ የኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጄኒ ቴሬክሂን በበኩላቸው፤ ሩሲያ ላለፉት አሥርተ ዓመታት በዘርፉ ያካበተችውን እውቀትና ልምድ ለኢትዮጵያ እና ለሌሎችም የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0