ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ፍትሕ የማስፈንና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሚናውን እያጣ ነው - ሊባኖሳዊ ባለሙያ
11:58 15.04.2026 (የተሻሻለ: 12:34 15.04.2026)
ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ፍትሕ የማስፈንና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሚናውን እያጣ ነው - ሊባኖሳዊ ባለሙያ
— Sputnik Ethiopia (@sputnik_ethio) April 15, 2026
⚖️ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት "በመርጦ አልቃሽ ፍትሑ" ተቀባይነቱን እያጣ መሆኑን የወንጀል ፍትሕ ባለሙያው ኦማር ናሻቤህ… pic.twitter.com/cOVGf1dUas
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ፍትሕ የማስፈንና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሚናውን እያጣ ነው - ሊባኖሳዊ ባለሙያ
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት "በመርጦ አልቃሽ ፍትሑ" ተቀባይነቱን እያጣ መሆኑን የወንጀል ፍትሕ ባለሙያው ኦማር ናሻቤህ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ባለሙያው "የተመረጠ ፍትሕ እውነተኛ ፍትሕ አይደለም" ብለዋል።
የሮም ሕግ ፈራሚ የሆኑ የአውሮፓ ሀገራት ለፍርድ ቤቱ ድጋፍ የሚሰጡት ጉዳዮቹ ከፖለቲካ ፍላጎታቸው ጋር ሲጣጣሙ ብቻ እንደሆነ ገልጸው፤ ይህ ካልሆነ ግን ድጋፋቸውን በመንፈግ ተቋሙ ከፍትሕ ይልቅ ወደ ፖለቲካዊ አካልነት እንደቀየሩት ጠቁመዋል።
ፍርድ ቤቱ የመጀመሪያ ሥልጣኑ ፍትሕን ማረጋገጥ ቢሆንም የውጭ ጫናዎች የተቋሙን ተዓማኒነትና ውጤታማነት አዳክመው ተቀባይነቱን እንዳሳጡት ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ሕግ ካሪም ካን ላይ የቀረበውን የጾታዊ ትንኮሳ ክስ ያነሱት ናሻቤህ፤ አንድ ዓለም አቀፍ አቃቤ ሕግ ከማንኛውም ነቀፋ የጸዳ መሆን ስላለበት እንዲህ ያሉ ክሶች መቅረባቸው በራሱ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ የምርመራ ውጤቱ በፍርድ ቤቱ ውስጥ ውስጣዊ አለመግባባቶችን በመፍጠሩ የአይሲሲን ተዓማኒነት ይበልጥ እንዲሸረሸር አድርጎታል።
የፍርድ ቤቱ አባል ሀገራት በካሪም ካን ላይ የቀረቡት ሁለት የጾታዊ ጥቃት ክሶችን የተመለከቱ ሪፖርቶች ከደረሷቸው በኋላ በጉዳዩ ላይ የሚደረገው ምርመራ እንዲቀጥል በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ድምጽ መስጠታቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ተንቀሳቃሽ ምሥል
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X