ሩሲያ እና ቻይና በሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ምክንያት የሚከሰተውን የነዳጅ ቀውስ የመከላከል አቅም አላቸው - ላቭሮቭ
ሩሲያ እና ቻይና በሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ምክንያት የሚከሰተውን የነዳጅ ቀውስ የመከላከል አቅም አላቸው - ላቭሮቭ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቻይና መሪ ሺ ጂንፒንግ ጋር ከተወያዩ በኋላ የሰጧቸው ተጨማሪ መግለጫዎች፦
◻ ሩሲያ በሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ምክንያት በቻይና እና በሌሎች ሀገራት ላይ የሚከሰተውን የኢነርጂ እጥረት የመሙላት አቅም አላት።
◻ ፕሬዚዳንት ፑቲን በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ በቻይና ጉብኝት ያካሂዳሉ።
◻ አሜሪካ እና ኢራን ለድርድራቸው ተጨባጭ ግቦችን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤ ሩሲያ እና ቻይና ለየትኛውም ዓይነት የውጭ ድጋፍ ዝግጁ ናቸው።
◻ ሞስኮ ኢራን የበለጸገ ዩራኒየሟን በተመለከተ የምታሳልፈውን የትኛውንም ውሳኔ ትቀበላለች፤ ለጉዳዩ እልባት አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ናት።
◻ የሩሲያ እና አሜሪካ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አልተቋረጠም፤ ግንኙነቶች ይፋ ባይሆኑም አሁንም ቀጥለዋል።
◻ በአላስካ በዩክሬን ጉዳይ የተደረጉ ውይይቶች ትኩረታቸው በመሬት ላይ ላለው ነባራዊ ሁኔታ ሕጋዊ እውቅና መስጠት ነበር፤ ሞስኮ በጉባኤው ላይ ለተደረሱ ስምምነቶች ታማኝ ናት።
◻ አሜሪካ በሩሲያ ላይ የጣለቻቸው ማዕቀቦች እንዲሁም በገበያው ውስጥ በሩሲያ የኢነርጂ ኩባንያዎች ላይ የሚፈጸመው አድሎአዊ አሠራር እንደቀጠለ ነው።
◻ ምዕራባውያን ዩክሬን ዋና አባል የምትሆንበት አዲስ ወታደራዊ ግንባር ለመፍጠር እያሰቡ ነው።
◻ ኢማኑኤል ማክሮን በዩክሬን ውስጥ "የማረጋጋት ኃይል" የመመስረት ሐሳብን ይደግፋሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X