አዲስ አበባ ከአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ባለፈ የአኅጉሪቱ የባሕል መዳረሻ ሆናለች - የሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል
10:54 15.04.2026 (የተሻሻለ: 11:07 15.04.2026)

ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ ከአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ባለፈ የአኅጉሪቱ የባሕል መዳረሻ ሆናለች - የሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል
ወርልድ ፒፕልስ አሴምብሊ የተሰኘ ተቋም ከሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል ጋር በመተባበር የአፍሪካ ሴቶች የሥነ-ጥበብ ሽልማት የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች የስዕል ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ አዘጋጅቷል።
አውደ ርዕዩን በንግግር የከፈቱት የሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል ዳይሬክተር ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ፤ “አዲስ አበባ ከአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ባሻገር የአኅጉሪቱ የባሕል መዳረሻ ሆናለች” ብለዋል።
አውደ ርዕዩ አፍሪካውያን የባሕል እና የሥነ-ጥበብ እሴቶቻቸውን በመለዋወጥ አብሮነትን እንዲያጠናክሩ እድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ፣ ናይጀሪያ እና ናሚቢያን ጨምሮ ከአስር የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ አርባ ሴት ተወዳዳሪዎች የስዕል ሥራዎቻቸውን እንዳቀረቡ የወርልድ ፒፕልስ አሴምብሊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አማካሪ ያኒና ዱበይካቭስካያ ገልጸዋል።
ለውድድሩ ፍጻሜ የደረሱት ሴት ሰዓልያን ከማክሰኞ ሚያዝያ 6፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው አውደ ርዕይ ላይ ሥራዎቻቸውን ለእይታ ያበቃሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X