ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረሙ

ሁለቱ ሀገራት በትምህርት፣ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ያተኮሩና ለወደፊት ትብብር እንደ ስትራቴጂካዊ መሠረት እና ተግባራዊ ፍኖተ-ካርታ የሚያገለግሉ ስምምነቶችን እንደተፈራረሙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀደም ብለው ከላይቤሪያ ፕሬዚደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

"ውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች ያለንን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍ ከፍቷል" ሲሉ በማኅበራዊ ገጻቸው ገልጸዋል።



የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የማጠናከር ዓላማ አለው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0