ኬንያ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት በዓመት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ልታጣ ትችላለች ተባለ

ሰብስክራይብ

ኬንያ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት በዓመት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ልታጣ ትችላለች ተባለ

የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት እንዳመለከተው፤ የአሜሪካ እና ኢራን ግጭት በቀጣናው የኬንያውያን ሠራተኞችን የሥራ ዕድል እየሳጣ በመሆኑ፤ ሀገሪቱ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት በተለይም ከሳዑዲ አረቢያ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፤ በየዓመቱ የምታገኘውን ከ480 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሐዋላ ገቢ ልታጣ ትችላለች።

"ኢስትሌይ ቮይስ" የዘገበውን ሪፖርት ጠቅሶ እንደገለፀው፤ ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ በየወሩ ወደ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ አደጋ ላይ ይወድቃል።

⬇ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የነዳጅ ዋጋ መጨመር የትራንስፖርት እና የምርት ወጪን ከፍ በማድረጉ፤ የኬንያ የግል ዘርፍ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጋቢት ወር መኮማተር አሳይቷል።

የባህረ ሰላጤው ሀገራት ለኬንያ የመሠረተ ልማት እና የኢነርጂ ግዢ ቁልፍ የገንዘብ ምንጮች መሆናቸውን ሪፖርቱ ጠቁሞ፤ ይህም ሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ ለሚቆይ ቀጣናዊ አለመረጋጋት ይበልጥ ተጋላጭ እንድትሆን አድርጓታል ብሏል። ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ጫና ውስጥ ሊከት እንደሚችልም ተገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0