ዚምባብዌ የኢኮኖሚ መረጋጋት እና የኢንዱስትሪ ጥንካሬ ምልክቶች እያሳየች መሆኑን የዓለም ባንክ ሪፖርት አመለከተ
18:59 14.04.2026 (የተሻሻለ: 19:04 14.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ የኢኮኖሚ መረጋጋት እና የኢንዱስትሪ ጥንካሬ ምልክቶች እያሳየች መሆኑን የዓለም ባንክ ሪፖርት አመለከተ
የዓለም ባንክ የ2026 የፀደይ ወቅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትንበያ እንደሚያሳየው፤ ሀገሪቱ አዎንታዊ የበጀት ሚዛን እና ፈጣን የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ምልክቶች አሳይታለች።
እ.ኤ.አ በ2025 የሀገሪቱ የበጀት ትርፍ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 0.4 በመቶ በመድረስ ከቀጣናው አማካይ የ3.3 በመቶ የበጀት ጉድለት የተሻለ አፈፃጸም አስመዝግቧል።
የዋጋ ግሽበትም ቀደም ሲል ከነበረበት ባለ ሦስት አሃዝ በመውረድ እ.ኤ.አ ከየካቲት 2026 ጀመሮ ከዓመት እስከ ዓመት እጅግ በጣም ቀንሶ 3.8 በመቶ ደርሷል።
ሪፖርቱ በተጨማሪም ዚምባብዌን ከደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና ኬንያ ጋር የኢንዱስትሪ ፖሊሲ መሳሪያዎችን በንቃት ከሚጠቀሙ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ መድቧታል፡፡ ይህም ሀገሪቱ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ያላትን ፍላጎት እንደሚያሳይ ጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X