ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያቸውን አክሲዮን በተለያዩ የአፍሪካ የገበያ ማዕከላት ሊያቀርቡ ነው
18:25 14.04.2026 (የተሻሻለ: 18:34 14.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያቸውን አክሲዮን በተለያዩ የአፍሪካ የገበያ ማዕከላት ሊያቀርቡ ነው
የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ አክሲዮኖች በአፍሪካ የአክሲዮን ገበያዎች ሲቀርቡ በአኅጉሪቱ የመጀመሪያው ይሆናል ሲሉ የናይሮቢ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ኃላፊ ገልፀዋል።
በቀን 650 ሺህ በርሜል የማጣራት አቅም ያለውና በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን አቅም ወደ 1.4 ሚሊዮን በርሜል ለማሳደግ ታቅዷል።
አኅጉር አቀፍ የሆነው የመጀመሪያ ደረጃ የሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ ቀጣናዊ የካፒታል ገበያዎችን እንደሚያጠናክር የሚጠበቅ ሲሆን የማዳበሪያ ምርትን በአራት እጥፍ ማሳደግን ጨምሮ የፔትሮኬሚካል ማጣሪያ ፋብሪካውን የ40 ቢሊዮን ዶላር የእድገት ውጥን በገንዘብ እንደሚረዳ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች አመልክተዋል።
ዳንጎቴ የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን የሚያግዙ እንደ ስታንቢክ አይ.ቢ.ቲ.ሲ ካፒታል፣ ቬቲቫ አድቫይዘሪ ሰርቪስ እና ፈርስት ካፕ ያሉ አማካሪዎችን ቀጥሯል። ኩባንያው ከአክስዮን ገበያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አረጋግጧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X