የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት "በየትኛውም ሰዓት ዳግም ሊያገረሽ ይችላል" - አልጄሪያዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት "በየትኛውም ሰዓት ዳግም ሊያገረሽ ይችላል" - አልጄሪያዊ ባለሙያ

የጸጥታ ጉዳዮች ባለሙያ እና የ "Menadefense" ድረ-ገጽ መስራች አክራም ካሪፍ፤ በተለይም ዋሽንግተን ለአዲስ ጥቃቶች ለመዘጋጀት ድርድሮችን የምታጓትት ከሆነ ሁኔታው የማያስተማምን ሆኖ ይቆያል ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በተለይ የአሜሪካ ማዕቀቦች እና የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ገደቦች ከቀጠሉ፤ ኢራን የተራዘመ እና አስቸጋሪ የመልሶ ግንባታ ሂደት እንደሚጠብቃት ገልጸዋል።

ሆኖም ኢራን እንደ "ሻሄድ" አይነት ድሮኖች ላይ በከፍተኛው ኢንቨስት በማድረግ፤ ብዛት እና ቅለትን ምርጫዋ ማድረጓን ባለሙያው አፅንዖት ሰጥተዋል።

ካሪፍ አክለውም "ኢራናውያን ከሞላ ጎደል ለመከተል የመረጡት መርህ ይህ ነው። የሲቪል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፤ በቴክኖሎጂ ደረጃቸው ውስን የሆኑ ነገር ግን በብዛት እና በጣም በዝቅተኛ ወጪ የሚመረቱ ድሮኖችን መገንባት ነው" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0