ጂቡቲ ለኢትዮጵያ ያቀረበችው የወደብ ባለቤትነት ድርሻ ውል ውድቅ መደረጉን ገለጸች

ጂቡቲ፣ ኢትዮጵያ
ጂቡቲ፣ ኢትዮጵያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2026
ሰብስክራይብ
ጂቡቲ ለኢትዮጵያ ያቀረበችው የወደብ ባለቤትነት ድርሻ ውል ውድቅ መደረጉን ገለጸች

የኢትዮጵያ መንግሥት በታጁራ ወደብ የቀረበለትን የ60 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሳይቀበል መቅረቱን የጂቡቲ የወደቦችና የነፃ ቀጣና ባለሥልጣን አስታውቋል።


"ያቀረብነው በታጁራ ወደብ 60 በመቶ ድርሻ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ከባለቤትነት ድርሻው በተጨማሪ ኮሪደር በመፈለጉ ጥያቄውን ሳይቀበለው ቀርቷል" ሲሉ የጂቡቲ የወደቦችና የነፃ ቀጣና ባለሥልጣን ሰብሳቢ አቡበከር ኦማር ሀዲ መናገራቸውን የግል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።


ጂቡቲ አሁንም ለኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ንግድ ክፍት መሆኗን የገለጹት ሰብሳቢው፤ በተለይም እንደ ማዳበሪያ ላሉ ስትራቴጂካዊ ጭነቶች ቅድሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

ጂቡቲ አማራጩን ያቀረበችው ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ በቀጣናው የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ ነው። ሆኖም የኮሪደር ጥያቄው ድርድሩን እንዳስተጓጎለው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0