ግብፅ ከሩሲያ ክልሎች ጋር ትብብሯን የማስፋት እቅድ እንዳላት ገለጸች
16:02 14.04.2026 (የተሻሻለ: 16:04 14.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ግብፅ ከሩሲያ ክልሎች ጋር ትብብሯን የማስፋት እቅድ እንዳላት ገለጸች
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር የታታርስታን ኩባንያዎች በልዩ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ የተለየ ጥቅም ሊያገኙ ይችላሉ ማለታቸውን የሩሲያ የታታርስታን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሩስታም ሚኒካኖቭ በግብፅ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የሪፐብሊኩ የፕሬስ አገልግሎት ገልጿል።
የታታርስታን ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፤ ግብፅ በበርካታ የኢንዱስትሪ እና ኢነርጂ ዘርፍ የጋራ ፕሮጀክቶች የሩሲያ ወሳኝ የንግድ አጋር መሆኗን ገልጸዋል። የታታርስታን ሪፐብሊክ እነዚህን ግንኙነቶች በማጠናከር ረገድ ንቁ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑን እና ከእስልምናው ዓለም አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛነቷን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ቪዲዮው ሚኒካኖቭ በግብፅ ጉብኝታቸው ወቅት ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉትን ውይይት ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X