የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ በፈጠረው መስተጓጎል የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ማዕድን አውጪዎች የኬሚካል አጠቃቀማቸውን ቀነሱ

የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት
የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2026
ሰብስክራይብ
የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ በፈጠረው መስተጓጎል የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ማዕድን አውጪዎች የኬሚካል አጠቃቀማቸውን ቀነሱ

በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት የኬሚካል አቅርቦቶችን በማስተጓጎሉ፤ ግንባር ቀደም የኮንጎ የኮፐር እና የኮባልት አምራቾች ማዕድናቱን ለማቅለጥ የሚጠቀሙባቸውን ቁልፍ ኬሚካሎች አጠቃቀም ለመቀነስ ተገደዋል።

አንዳንድ ኩባንያዎች በዚህ ወር የትዕዛዝ ስረዛ ያጋጠማቸው ሲሆን አሁን ደግሞ የምርት መጠን ለመቀነስ እያጤኑ መሆኑን የብሪታንያ መገናኛ ብዙኃን የዘርፉን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።

ℹ የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች በከፍተኛ ሁኔታ በሰልፈሪክ አሲድ ላይ ጥገኛ ናቸው። በኢስላማባድ የተካሄደው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ አሜሪካ ሆርሙዝን ለመዝጋት በማስፈራራቷ በሰርጡ የሚያልፉ ጭነቶች መስተጓጎል ተጋርጦባቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0