የፖሊሲዎች አለመጣጣምና የአሠራሮች አለመቀናጀት የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ ዕድገት ገድቦታል ተባለ

የአፍሪካ የግብርና ዘርፍ
 የአፍሪካ የግብርና ዘርፍ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2026
ሰብስክራይብ
የፖሊሲዎች አለመጣጣምና የአሠራሮች አለመቀናጀት የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ ዕድገት ገድቦታል ተባለ

ይህ የተባለው በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት ከፍተኛ ጉባኤ ላይ ነው።


ጥምረቱ የተመሰረተበትን 20ኛ ዓመት ታሳቢ አድርጎ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጥምረቱ የቦርድ ሰብሳቢ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ “የአፍሪካ ፈተና የመፍትሄ እጦት ሳይሆን የፖሊሲዎች አለመጣጣምና የአሠራሮች አለመቀናጀት ነው” ብለዋል።


በመሆኑም የአኅጉሪቱን የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ የተቀናጁና ውጤታማ የልማት ስትራቴጂዎችና ፖሊሲዎች እንደሚያስፈልጉ፤ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት መነሻ አድርገው ተናግረዋል።

ጉባኤው የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ስኬቶች መነሻ በማድረግ የአፍሪካን ግብርና ማሸጋገርና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ይመክራል ሲል የዘገበው የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0