የ25 ቢሊዮን ዶላር የናይጄሪያ-ሞሮኮ የጋዝ መስመር ዝርጋታ ስምምነት በዚህ ዓመት ይፈረማል - የሞሮኮ የሃይድሮካርቦን ኤጀንሲ

የናይጄሪያ-ሞሮኮ የጋዝ መስመር
 የናይጄሪያ-ሞሮኮ የጋዝ መስመር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2026
ሰብስክራይብ
የ25 ቢሊዮን ዶላር የናይጄሪያ-ሞሮኮ የጋዝ መስመር ዝርጋታ ስምምነት በዚህ ዓመት ይፈረማል - የሞሮኮ የሃይድሮካርቦን ኤጀንሲ

የሞሮኮ የሃይድሮካርቦን እና ማዕድን ኤጀንሲ ኃላፊ አሚና ቤንካድራ ለብሪታንያ የዜና ወኪል እንደገለጹት፤ በ6,900 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ በባሕርና በየብስ የሚዘረጋው የአፍሪካ አትላንቲክ ጋዝ መስመር በዓመት እስከ 30 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ጋዝ የማስተላለፍ አቅም ይኖረዋል።

በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ፕሮጀክት፤ የአዋጭነት ጥናትና የቅድመ-ምህንድስና ዲዛይን ሥራዎቹ ተጠናቀዋል።

ናይጄሪያ ፕሮጀክቱን ለማስተናበር ከ13 ተሳታፊ ሀገራት የተወከሉ አባላት ያሉበት የጋራ ባለሥልጣን እንደምታቋቁም ቤንካድራ ገልጸዋል፡፡

የሞሮኮ ኦንህይም እና ኤንኤንፒሲ የጋራ ኩባንያ ደግሞ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም፣ ፋይናንስ እና ግንባታ በበላይነት ይቆጣጠራል።

የጋዝ መስመሩ ዓላማዎች፡-

የኃይል ማመንጫዎችን፣ ኢንዱስትሪዎችን እና የማዕድን ቁፋሮዎችን በመደገፍ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር፣

የሞሮኮን አፍሪካ እና አውሮፓን በኃይል የማገናኘት ሚና ማጎልበት።

ዝርጋታው በመጀመሪያ ምዕራፎች ሞሮኮን ከሞሪታኒያ እና ሴኔጋል፤ በመቀጠል ጋናን ከኮትዲቯር ጋር በማስተሳሰር በሂደት እስከ ናይጄሪያ የጋዝ ማውጫዎች ይደርሳል።

1⃣ የመጀመሪያው የጋዝ ምርት ለተጠቃሚዎች መድረስ የሚጀምረው እ.ኤ.አ በ2031 ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0