ሮሙዋልድ ዋዳግኒ የቤኒን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን እንዳሸነፉ ግዜያዊ ውጤት አመለከተ
የቤኒን መንግሥት የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ዋዳግኒ 94.05 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ገለልተኛ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ሰኞ ምሽት ባወጣው ጊዜያዊ ውጤት አስታውቋል።
ዋዳግኒ የተመረጡት ለሰባት ዓመታት የሥልጣን ዘመን ነው።
ተቀናቃኛቸው የቀድሞው የባሕል ሚኒስትር ፖል ሁንክፔ 5.95 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል።
ሁንክፔ የምርጫው ውጤት ይፋ ከመደረጉ በፊት ሽንፈታቸውን አምነው ብቸኛ ተቃዋሚ ለነበሩት ዋዳግኒ "ሪፐብሊካዊ የእንኳን ደስ አለዎት" መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኮሚሽኑ ይፋ የተደረገው ውጤት ጊዜያዊ ሲሆን በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት መሠረት በሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት መጽደቅ ይኖርበታል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X