አሜሪካ ተጨማሪ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ተኩስ አቁሙን "ኃይል ለማሰባሰብ" እንደ ጥሩ አጋጣሚ እየተጠቀመችበት ነው - ግብፃዊ ወታደራ ባለሙያ
አሜሪካ ተጨማሪ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ተኩስ አቁሙን "ኃይል ለማሰባሰብ" እንደ ጥሩ አጋጣሚ እየተጠቀመችበት ነው - ግብፃዊ ወታደራ ባለሙያ
ብሪጋዴር ጄኔራል ሳሚር ራጊብ ለስፑትኒክ እንደገለጹት፣ ወታደራዊ ዝግጅቱ የጦር መሣሪያዎችን፣ ሚሳኤሎችን እና ጥይቶችን ማሰባሰብን ያካትታል።
እንደ ራጊብ ትንታኔ፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለው ሁኔታ በሚከተለው መልኩ ሊቀጥል ይችላል፦
አውሮፓ የባህር ላይ እገዳውን ልትቀላቀል የምትችለው የመርከቦችን ደህንነት ለማረጋገጥ ብቻ እንጂ በውጊያ ውስጥ ለመሳተፍ ላይሆን ይችላል፡፡
የባህር ወሽመጡ በስምምነት፣ በጫና ወይም በድርድር ክፍት ከሆነ፣ የኒውክሌር ስምምነት ላይ እስከሚደረስ ድረስ ግጭቱ በነበረበት ይቆማል፡፡
ኢራን ወሽመጡን ለመዝጋት ኃይል የምትጠቀም ከሆነ፣ ግጭቱ ወደ ከተኩስ አቁሙ በፊት ወደነበረበት ሁኔታ ይመለሳል፡፡
ኢራን የባህር ላይ እገዳውን ለአጭር ጊዜ መቋቋም ብትችልም፣ የረጅም ጊዜ እገዳ ግን ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይከታታል።
ባለሙያው አክለውም፣ በአሜሪካ እይታ "የመድር (የእግረኛ) ወረራ" እንደ አንድ አማራጭ ቢታይም፣ ጦርነቱ በዚህ መልክ አይቀጥልም። ይልቁንም አሜሪካ ሌሎች አማራጮችን በዋናነት እገዳን ትመርጣለች። ይህም በሚቀጥሉት ቀናት የቦምብ ጥቃቶች ወይም ግጭቶች ከተከሰቱ በአካባቢው ላይ ትልቅ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል።
ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች የተገኘ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X