የቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአስር ቀናት የአፍሪካ ጉዟቸውን ጀመሩ
18:33 13.04.2026 (የተሻሻለ: 18:44 13.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአስር ቀናት የአፍሪካ ጉዟቸውን ጀመሩ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በአልጄሪያ፣ ካሜሩን፣ አንጎላ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ የሚገኙ 11 ከተማዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብደልማጅድ ተቡኔ አቀባበል የተደረገላቸው ቅዱስነታቸው፣ አልጄሪያ ለነፃነት፣ ለሉዓላዊነት እና ለክብር ባደረገችው ተጋድሎ ለወደቁ ሰማዕታት ከመታሰቢያ ሐውልታቸው በመገኘት ክብር ሰጥተዋል። እውነተኛ ሰላም "የፍትህ እና የክብር መገለጫ" እንደሆነና "ሊገኝ የሚችለውም በይቅርታ ብቻ" እንደሆነም አጉልተዋል።
የቫቲካን ከፍተኛ ባለስልጣን ካርዲናል ማይክል ቼርኒ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ የጉብኝቱ ዓላማ "ከ20 በመቶ በላይ ካቶሊኮች በሚኖሩባት አኅጉር ላይ የዓለምን ትኩረት ለማሳረፍ" ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጉዟቸው ወቅት ትኩረት የሚሰጧቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፡-
🟠 ሰላም፣
🟠 ስደት፣
🟠 የአካባቢ ጥበቃ እና
🟠 ወጣቶች እና ቤተሰብ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X