በነጻ የንግድ ቀጠና ዞኖች ምርት የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል - ገንዘብ ሚኒስቴር

በነጻ የንግድ ቀጠና ዞኖች ምርት የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል
በነጻ የንግድ ቀጠና ዞኖች ምርት የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.04.2026
ሰብስክራይብ
በነጻ የንግድ ቀጠና ዞኖች ምርት የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል - ገንዘብ ሚኒስቴር

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ በአዲሱ አሰራር መሠረት በነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ ምርት የሚያመርቱ ባለሀብቶች ምርቱን ለገበያ ሲያቀርቡ ብቻ ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

ይህ ማበረታቻ የንግድ ቀጠናዎችን ለባለሀብቶች ይበልጥ ሳቢ ለማድረግና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ሊጠቀሱ የሚችሉ ምክንያት መሆናቸውን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል ብሏል።

ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ያላትን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና አገሪቱን የአፍሪካ የንግድና የሎጂስቲክስ ማዕከል ለማድረግ የታለመ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0