የሩሲያ ጂምናስቲክ ተወዳዳሪዎች በኡዝቤኪስታን የ"ሪዝሚክ" ጂምናስቲክስ የዓለም ዋንጫ አራት ሜዳሊያዎችን አሸነፉ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ጂምናስቲክ ተወዳዳሪዎች በኡዝቤኪስታን የ"ሪዝሚክ" ጂምናስቲክስ የዓለም ዋንጫ አራት ሜዳሊያዎችን አሸነፉ

ማሪያ ቦሪሶቫ በሁሉም ዘርፍ የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም በ"ሁፕ" የብር ሜዳሊያ አሸንፋለች።

በቡድን ውድድር፣ አሌና ሴሊቨርስቶቫ፣ አሊና ፕሮሽቻሊኪና፣ ዝላታ ሬምቹኮቫ፣ ኔሊ ሬውትስካያ እና ኒኮል አንድሮንቺክ በአምስት ሪባን ውድድር ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም "በሁፕ እና ክለብስ" ደግሞ ሦስተኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡


​"ሁሉም የጂምናስቲክ ተወዳዳሪዎች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፋቸውና የውድድር ልምድ ማግኘታቸው በጣም አስፈላጊ ነው" ሲሉ
አሰልጣኝ ታቲያና ሰርጋዬቫ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።


በታሽከንት የተካሄደው፣ የሪዝሚክ ጂምናስቲክስ የዓለም ዋንጫ እሁድ ተጠናቋል። ሩሲያውያን አትሌቶች ገለልተኛ (ሀገራትን የማይወክሉ) በመሆን ነበር በውድድሩ የተሳተፉት፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0