ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ በአፍሪካ ራስን መቻልና ትብብር ዙሪያ ተወያዩ

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ በአፍሪካ ራስን መቻልና ትብብር ዙሪያ ተወያዩ
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ በአፍሪካ ራስን መቻልና ትብብር ዙሪያ ተወያዩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ በአፍሪካ ራስን መቻልና ትብብር ዙሪያ ተወያዩ

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ፣ ከአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚምባንክ) ፕሬዝዳንት ዶክተር ጆርጅ ኤሎምቢ ጋር መወያየታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በውይይታቸውም፣ ክልላዊ ትስስርን በማጠናከር፣ የአኅጉሪቱን የውስጥ ንግድን በማስፋፋት እና የአፍሪካን የፋይናንስ ሀብቶች በከፍተኛ ሁኔታ በማንቀሳቀስ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ጥንካሬ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም፣ የአቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥ ያሉ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም በአፍሪካ የተቀናጀ ምላሽ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ኃላፊዎቹ መሠረታዊ የሸቀጦች አቅርቦትን ለማረጋጋት እና የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመጠበቅ በሚረዱ አኅጉራዊ ተነሳሽነቶች ላይ ሐሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

በኢንዱስትሪ፣ የፋይናንስ መሰረተ ልማት እና በፋይናንስ ዘርፍ (በቀጣናዊ የክፍያ እና የሂሳብ ማወራረጃ ስርዓቶች) ላይ ተቋማቱ ተቀራርበው መሥራት ይገባቸዋል ተብሏል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0