ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እንድታደርግ ተጠየቀች – ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እንድታደርግ ተጠየቀች
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እንድታደርግ ተጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሲቪል አቪዬሽን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እንድታደርግ ተጠየቀች – ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን

በልምድ ልውውጥና የእውቀት ሽግግር፣ በአቪዬሽን ደህንነት እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ድጋፎች እንዲደረግላት ጥያቄ ማቅረቧን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

የሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን ልዑካን ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ አበራ ጋር በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ትራንስፖርት ሚኒስቴር ምክትል ዋና ፀሐፊ ፖል ቼል ገም፣ ድጋፉን ተግባራዊ ለማድረግ የሁለትዮሽ የአየር አገልግሎት ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ለመፈራረም እንደሚፈልጉ አብራርተዋል፡፡


ዮሐንስ አበራ በበኩላቸው፣ “ጠንካራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሌላት ሀገር ጠንካራ አየር መንገድ ሊኖራት አይችልም፤ እኛ ከዚህ አንፃር ከ80 ዓመታት በላይ ልምድ ያለን በመሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደምናደርግላችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡” ብለዋል፡፡


ሁለቱ ወገኖች የአየር አገልግሎት ስምምነት በቅርቡ እንደሚፈራረሙ ከውይይታቸው መረዳት እንደተቻለም ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0