በኡጋንዳ የሚገኙ ቺምፓንዚዎች ረጅም ጊዜ የፈጀ 'የእርስ በርስ ጦርነት' ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ
18:02 12.04.2026 (የተሻሻለ: 18:04 12.04.2026)
ሰብስክራይብ
በኡጋንዳ የሚገኙ ቺምፓንዚዎች ረጅም ጊዜ የፈጀ 'የእርስ በርስ ጦርነት' ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ
በኡጋንዳ ኪባሌ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኝ የቺምፓንዚዎች ማኅበር (መንጋ) እ.አ.አ በ1995 ለሁለት ከተከፈለ በኋላ በቀጠለ ግጭት ውስጥ እንደሚገኝ ከቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ የጥናት ቡድን አስታውቋል።
ፀቡ በተለይ እ.አ.አ በ2014 ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያቶች ናቸው የተባሉ ነጥቦች በጥናቱ ተለይተዋል፦
🟠 የምግብ ፉክክር፣ በቡድኑ አባላት ብዛት ምክንያት የተፈጠረ ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣
🟠በወንዶቹ መካከል የመራባት ፉክክር፣
🟠 የማኅበራዊ ትስስር መቋረጥ፣ በእ.ኤ.አ በ2014 በርካታ ጎልማሳ ወንድ እና አንዲት ሴት ቺምፓንዚዎች መሞት ማኅበራዊ ትስስሩን ማናግት፣
🟠 የመሪ ለውጥ፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 2015 የተደረገው የቡድን መሪ ለውጥ ጥቃቶችን ሊያባብስ መቻሉ፣
🟠 የመተንፈሻ አካል ወረርሽኝ፣ 25 ቺምፓንዚዎችን የገደለ ወረርሽኝ መከሰቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X