​በበጀት ዓመቱ 8 ወራት በኢንዱስትሪ ተኪ ምርቶች 4.2 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
​በበጀት ዓመቱ 8 ወራት በኢንዱስትሪ ተኪ ምርቶች 4.2 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

በዚህ ወቅት ለተመዘገበው ገቢ “የኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ላይ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲመጣ ማድረጉ ተገልጿል።

​የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ቁጥር በ2010 የበጀት ዓመት ከነበረበት 18,747 በአሁኑ ወቅት ወደ 27,764 ከፍ ማለቱ በኢንዱስትሪ መስፋፋት ረገድ የታየውን ተከታታይ ዕድገት እንደሚያሳይ መገለጹን የሚኒስቴሩን ባለሥልጣን ጠቅሶ የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

​በ2014 ዓ.ም ወደ 46 በመቶ ዝቅ ብሎ የነበረው የማምረት አቅም አሁን ላይ ወደ 66.3 በመቶ ማሳደግ ተችሏል ተብሏል፡፡ የዘርፉ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ ባለፈው የበጀት ዓመት ከነበረበት 41.1 በመቶ ወደ 45.82 በመቶ ማደጉንም ዘገባው ጠቅሷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0