በአፍሪካ የጠፈር ኢንዱስትሪ የወደፊት ተስፋ እና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? ናይጄሪያውያን ተማሪዎች ያብራራሉ
18:28 11.04.2026 (የተሻሻለ: 18:34 11.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአፍሪካ የጠፈር ኢንዱስትሪ የወደፊት ተስፋ እና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? ናይጄሪያውያን ተማሪዎች ያብራራሉ
"በአፍሪካ የጠፈር ቴክኖሎጂ ጉዳይ በፍጥነት እያደገ ያለ የውይይት ርዕስ ነው። ብዙ እምቅ አቅሞችን እና እድገቶችን እያየን ነው። ከእንግዲህ ወደ ኋላ ልንሸሽ አንችልም፤ አይደል?" ሲል በአቡጃ የጠፈር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ ኢንስቲትዩት የጂኦ-ኢንፎርማቲክስ ተማሪ የሆነው ጆሹዋ ብራውን ለስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ሪዳ ቼቤት ተናግሯል።
በጆሹዋ ብራውን እና በኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ተማሪዋ ሳዲያ ሀሊማቱ ቢንዲር ገለጻ፣ አሁን ላይ በርካታ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የተጠቆመ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል፦
🟠 ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በመኖራቸው ምክንያት የሚታይ የገንዘብ ድጋፍ እጥረት፤
🟠 የመረጃ ክፍተቶች እና ከሳተላይቶች የሚገኙ ግዙፍ መረጃዎችን ለማስተናገድ የሚያስችሉ ዘመናዊ ሃርድዌሮች እና ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው የኮምፒውተር አቅሞች ዉሱንነት፤
🟠 የባለሙያዎች ፍልሰት፤ "በጠፈር ቴክኖሎጂ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በአፍሪካ ስነ-ምህዳር ውስጥ አለመቆየታቸው"፤
🟠 ትክክለኛ እና አካባቢያዊ የሆኑ መረጃዎች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ በተመለከተ በህዝቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ ማነስ።
የአፍሪካ የጠፈር ቴክኖሎጂ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ሊመስል እንደሚችል ተማሪዎቹ የሚያስቡትን ለመረዳት ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X