የአፍሪካ-ሩሲያ ግንኙነት ‘ሁለቱንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አጋርነት’ ነው - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ-ሩሲያ ግንኙነት ‘ሁለቱንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አጋርነት’ ነው - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ

​በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ኦስካር ቫን ሄርደን ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፣ ቀጥተኛ የሩሲያ-አፍሪካ የንግድ ልውውጥ እንደ ኤደን ባህረ ሰላጤ፣ ስዊዝ ካናል እና ሆርሙዝ ሰርጥ ያሉ "መረጋጋት የሌለባቸው ማነቆዎችን" በማስቀረት ወጪንና የማድረሻ ጊዜን ይቀንሳል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ የሩሲያ ቀጥተኛ አቅርቦቶች የሚሰጧቸው ቁልፍ ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው፦

🟠 የሩሲያ እህል እና ማዳበሪያ፣ የዋጋ ግሽበትን በመከላከል ቀውስ እንዳይከሰት ያደርጋሉ፡፡

🟠 የሩሲያ የጭነት መርከብ መስመር፣ የሩሲያ ወደቦችን ከደቡብ አፍሪካዋ ደርባን ጋር በቀጥታ በማገናኘት፣ አሁን ያለውን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር የሁለትዮሽ ንግድ በሦስት እጥፍ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

🟠  የሰሜን-ደቡብ ኮሪደር በማልማት ሩሲያ የአውሮፓ መተላለፊያዎችን በማስቀረት የደቡብ-ለደቡብ የንግድ ትስስር እንዲጎለብት ታደርጋለች፡፡

​🟠 ሩሲያ ለሽብርተኝነት መከላከያ የሚሆን የደህንነት ድጋፍ ትሰጣለች።

​"ሩሲያ በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የማትገባና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድጋፍ የምትሰጥ ተደርጋ ትታያለች። ከምዕራባውያን እርዳታ ጋር ተያይዘው ከሚመጡ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎች ነፃ ናት" ሲሉም ባለሙያው አክለዋል።

በተጨማሪም፣ ከሩሲያ ጋር ያለው ግንኙነት በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ አማራጮችንና ስልታዊ ዕድሎችን በመፍጠር፣ የአፍሪካን "የመደራደር አቅም" እንደሚያሳድግና "የምዕራባውያንን የበላይነት" እንደሚያመጣጥን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ሀገራት የሩሲያን ምርቶች በቀጥታ ለመቀበል ለምን ፍላጎት እንዳላቸው እና የትኞቹ ምርቶች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0