የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የጠፈር ሳይንስ ተቋማት በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የጠፈር ሳይንስ ተቋማት በትብብር ለመሥራት ተስማሙ
የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የጠፈር ሳይንስ ተቋማት በትብብር ለመሥራት ተስማሙ
 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.04.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የጠፈር ሳይንስ ተቋማት በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ፣ በሞስኮ ከሩሲያው 'ሮስኮስሞስ' ዋና ዳይሬክተር ዲሚትሪ ባካኖቭ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

አብዲሳ ይልማ በውይይታቸው ወቅት እንደተናገሩት፣ በተለይም በጠፈር መሠረተ-ልማት ግንባታ እና በባለሙያዎች ሥልጠና ዙሪያ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ሰፊ ልምድ ለመቅሰም ፍላጎት አላት።

ዲሚትሪ ባካኖቭ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያን የጠፈር ቴክኖሎጂ አቅም ለማጠናከር ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሁለቱም ወገኖች በዘርፉ የሁለትዮሽ ስምምነት መፈረም አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፣ ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣ በሞስኮ ቆይታቸው በሩሲያ የጠፈር ፎረም ላይ ተሳትፈዋል፡፡ የዓለም አቀፉን የጠፈር ጣቢያ የቁጥጥር ማዕከልንም ጎብኝተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0