በኢትዮጵያ የጋና ኤምባሲ እና ኩሪፍቱ ሪዞርት "የጋና ወር በኢትዮጵያ" የተሰኘ መርሃ ግብር በይፋ አስጀመሩ

"የጋና ወር በኢትዮጵያ"
የጋና ወር በኢትዮጵያ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.04.2026
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የጋና ኤምባሲ እና ኩሪፍቱ ሪዞርት "የጋና ወር በኢትዮጵያ" የተሰኘ መርሃ ግብር በይፋ አስጀመሩ

ከሚያዚያ 30 (ሜይ 8) እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ በኩሪፍቱ መንደር የሚቆየው መረሃ ግብር ባህላዊ ትርኢቶች፣ የፈጠራ ሥራዎች ዐውደ ርዕዮች እና የንግድ እንቅስቃሴዎች ይከናወኑበታል።


በኢትዮጵያ የጋና አምባሳደር ዶክተር ሮበርት አፍሪይ፣ መርሃ ግብሩ ከጋና የቱሪዝም፣ ሙዚቃ፣ የምግብ ጥበብ፣ አልባሳትና ታሪክን ጨምሮ የባህል ዲፕሎማሲ እንዲሁም የአኅጉራዊ አንድነት ራዕይ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ገልጸዋል።


አምባሳደሩ በጋና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እየጠነከረ መምጣቱንና ይህም በመላው አፍሪካ ሰላምንና ውህደትን ለማስፈን እንዲሁም የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን አፅንዖት መስጠታቸውን ኤምባሲው አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አስፈላጊነትን በማጉላት፣ "የጋና ወር" በባሕላዊ እና በሕዝብ ለሕዝብ የታገዘ የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ የሚጠቅም መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0