ዚምባብዌ የግብርና ክፍያዎችን እና ቀረጦችን ቀነሰች

ዚምባብዌ የግብርና ክፍያዎችን እና ቀረጦችን ቀነሰች
ዚምባብዌ የግብርና ክፍያዎችን እና ቀረጦችን ቀነሰች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.04.2026
ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ የግብርና ክፍያዎችን እና ቀረጦችን ቀነሰች

የንግድ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ ከሀገሪቱ ካቢኔ በተላለፈ መመሪያ መሠረት መንግሥት የሚከተሉትን እርምጃዎች ተግባራዊ አድርጓል፦

ለአነስተኛ አርሶ አደሮች የሚቀርቡ የማዳበሪያ እና አትክልትና ፍራፍሬ ክፍያዎች ቅናሽ ተደርጎላቸዋል፡፡

የራሳቸውን መሣሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገቡ አርሶ አደሮች የፈቃድ ግዴታ ተነስቶላቸዋል፡፡

በግድብ ግንባታ ላይ የግል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ደንቦች ተሻሽለዋል፡፡

የጥጥ ግዢ ቀረጥ ከ800 የአሜሪካ ዶላር ወደ 200 ዶላር ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

የዓሣ ምርት መሰብሰቢያ ክፍያዎች እንዲቀሩ ተደርጓል እንዲሁም

ለግብርና መሣሪያዎች መለዋወጫ የሚጠየቁ የገቢ ንግድ ፈቃዶች እንዲቀሩ ተደርጓል።


የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ምቱሊ ንኩቤ እንደተናገሩት፣ “ግብርና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፣ ለአገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 12 በመቶ ያህል፣ ለመደበኛው የሥራ ዕድል ከ30 በመቶ በላይ እንዲሁም ለኢንዱስትሪዎች ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውን ጥሬ ዕቃ ያቀርባል” ብለዋል።


እነዚህ ማሻሻያዎች ቢሮክራሲን ለመቀነስ፣ የእህል ዝውውርን ለማፋጠን እና የአልሚዎችን ፍላጎት ለማሳደግ ያለሙ ናቸው።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0