የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሁለት ምዕራፍ የሚተገበር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ግንባታን ይፋ አደረገ
13:22 10.04.2026 (የተሻሻለ: 13:24 10.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሁለት ምዕራፍ የሚተገበር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ግንባታን ይፋ አደረገ
10 ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት የመጀመሪያው ምዕራፍ፣ በአዲስ አበባ እና በአቅራቢያዋ ባሉ ከተሞች የ40 ጣቢያዎች ግንባታ የያዘ ሲሆን 3 ጣቢያዎች ከዚህ በፊት ተመርቀዋል።
እያንዳንዱ ጣቢያ በአንድ ጊዜ 24 ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም አለው። የአገልግሎት ክፍያው በኪሎ ዋት ሠዓት ከ14 እስከ 18 የኢትዮጵያ ብር ሆኖ ተቆርጧል።
የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታው ወደ ክልል ከተሞች (ቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ እና ሐዋሳ) እንደሚስፋፋ የአገልግሎቱን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጠቅሶ የውጭ ሚዲያ ዘግቧል።
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ሠዓሊተ ምህረት አካባቢ አስገንብቶ ሥራ ያስጀመረው ጣቢያ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X