ፓኪስታን እና ኢትዮጵያ የሦስትዮሽ የባህር ላይ ጥምረት ለመመሥረት እያጤኑ ነው ተባለ
12:13 10.04.2026 (የተሻሻለ: 12:22 10.04.2026)

ሰብስክራይብ
ፓኪስታን እና ኢትዮጵያ የሦስትዮሽ የባህር ላይ ጥምረት ለመመሥረት እያጤኑ ነው ተባለ
ፓኪስታን እና ኢትዮጵያ በእስያ እና አፍሪካ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ለማጎልበት ያለመ፣ ጅቡቲን የሚያካትት የሦስትዮሽ የባሕር (የማሪታይም) ጥምረት የመመሥረት እድልን ለመመርመር ተስማምተዋል፡፡ በጋራ ምክክር ላይ ተመስርቶ ተጨማሪ ሀገራትን እንዲያካትት ሊደረግ እንደሚችልም ተጠቁሟል።
የፓኪስታን የማሪታይም ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሐመድ ጁነይድ አንዋር እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላት ሀገር ብትሆንም፣ በተዋቀረ የማሪታይም ስምምነት የጅቡቲን ወደብ በመጠቀም የንግድ አቅሟን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ትችላለች፡፡ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ ይፋዊ ስምምነት ሊፈረም እንደሚችልም አክለዋል።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ዑመር ሁሴን በበኩላቸው፣ የቀረበውን ምክረ–ሐሳብ በመቀበል፤ በሁለቱም ወገኖች ባለሙያዎች መካከል ቴክኒካዊ ምክክሮች መደረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል ሲሉ የፓኪስታን ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X