ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ ቀጣናዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ ቀጣናዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራረሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተፈረሙ የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ታድመዋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ ናቸው ያላቸው ሁሉን አቀፍ ስምምነቶች የሚከተሉት ዘርፎች ያካተቱ ናቸው፡፡

መከላከያ፣
ጤና፣
ትምህርት፣
ውሃና ኢነርጂ፣
ግብርና፣
ንግድ፣
ዲጂታል መታወቂያ እና
ቱሪዝም

በሌላ በኩል፣ ኢቫሪስት ንድያይሺሚዬ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በመታሰቢያ ኃውልቱ ስርም የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0