ስልታዊ ውድቀት፦ አሜሪካ አሁን ለኢራን እጅ እየሰጠች ያለችበት ምክንያት

አሜሪካ አሁን ለኢራን እጅ እየሰጠች ያለችበት ምክንያት
አሜሪካ አሁን ለኢራን እጅ እየሰጠች ያለችበት ምክንያት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.04.2026
ሰብስክራይብ
ስልታዊ ውድቀት፦ አሜሪካ አሁን ለኢራን እጅ እየሰጠች ያለችበት ምክንያት

የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፕሮፌሰር ዶክተር አሲም ሳጃድ አክታር የኢራንን የ10 ነጥብ የእልባት እቅድ አስመልክቶ ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት፣ አሜሪካ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ስምምነቶችን (የኢራን ጥያቄዎችን ለመቀበል) ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

የኢራን ጥያቄዎች ትንኮሳ አልቦ ወረራዎች እንዳይካሄዱባት የሚጠይቅ ስምምነት፣ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኢራን ቁጥጥር ስር መሆን፣ ዩራኒየም የማበልጸግ ፈቃድ፣ ሁሉንም ማዕቀቦች ማንሳት፣ የተባበሩት መንግስታት እና የዓለምአቀፉን የኒውክሌር ውሳኔዎችን ማቋረጥ፣ የካሳ ክፍያ፣ የአሜሪካ ወታደሮች መውጣት እና በሁሉም ግንባሮች ላይ ጦርነት ማቆምን ያካትታሉ።

በአሜሪካ እና በኢራን ልዑካን መካከል የሚደረገው ድርድር ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ በኋላ በሚቀጥሉት ቀናት በኢስላማባድ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

አሜሪካ ያለችበትን ሁኔታ "በሁሉም ረገድ የታየ ስልታዊ ውድቀት" ሲሉ አክታር ሁኔታውን ያስረዳሉ።


​ "ዓለም ሁኔታውን የሚያየው በዚህ መንገድ ይመስለኛል፤ ኢራን ምንም እንኳን ትልቅ ዋጋ ብትከፍልም በመጨረሻ በድል አድራጊነት ወጥታለች" ብለዋል።



አክታር በአንዳንድ ማዕቀቦች ላይ የሚደረግ ማመቻመች ሊመጣ የሚችል ውጤት መሆኑን ለይተዋል። አሜሪካ አጠቃላይ የሆነ የማይነካኩ ዋስትና ትሰጣለች ብለው አያምኑም። አሜሪካ በዋነኝነት የምትፈልገው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ክፍት እንዲሆን ነው።

ባለሙያው አክለውም፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ደካማ መሆኑን እና እስራኤል በሊባኖስ ላይ የአየር ድብደባ በመፈጸም ስምምነቱን ለማደናቀፍ የተቻላትን ሁሉ እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0