አፍሪካ የመጻኢው ዘመን የዓለማችን ተስፋ ናት - ፕሮፌሰር ማሳምባ ካህ
አፍሪካ ያላትን ግዙፍ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሀብት ለሕዝቦቿ ብልጽግና እና ለዓለም አቀፍ መረጋጋት በትክክል ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባት በሞስኮ ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ሀገራት የኢንዱስትሪና ትምህርት አጋርነት ፕሮጀክት ኃላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ማሳምባ ተናግረዋል፡፡
“የአፍሪካ ህዳሴ፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እና የሀብት ተጠቃሚነት ይህንን አኅጉር ወደፊት የዓለም መሪ ማድረጉ የማይቀር ሀቅ ነው” ሲሉ ኃላፊው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡
አክለውም፤ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ከአፍሪካ ተቋማት ጋር በመተባበር ዕውቀትንና ክህሎትን ወደ አፍሪካ በማሸጋገር፤ ተማሪዎች በሀገራቸው ሆነው ለዘመናዊው ኢንዱስትሪ ብቁ እንዲሆኑ ማገዝ ይችላሉ ብለዋል።
አፍሪካ የኒውክሌር ኢነርጂን ለአስተማማኝ የኢኮኖሚ ዕድገት በአማራጭነት ማየት እንደሚኖርባትም አስረድተዋል።
“ሩሲያ፤ በመንግሥት ኮርፖሬሽን ሮሳቶም ልዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኢንተርፕራይዞች በሥልጠና አማካኝነት ዘላቂ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና አስተማማኝ የቴክኒክ መፍትሄዎችን ማምጣት የምትችል ሁነኛ አጋር ናት፡፡"
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X