ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግርን ከዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ጋር አጣጥማለች - የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግርን ከዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ጋር አጣጥማለች - የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

የአፍሪካ የአደጋ ስጋት አቅም አኅጉራዊ ጉባዔ የሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ዋጋ ከመረዳት ባለፈ፤ ተፅዕኖውንም በተግባር አይታለች ብለዋል።

“በመሆኑም የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የልማት ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ መርጠናል፡፡ ይህም ለብሔራዊ እድገትና ለዓለም አቀፋዊ ኃላፊነት ያለንን ቁርጠኝነት ያንጸባርቃል” ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገሪቱ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የማዕድን፣ የቱሪዝም እና የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች እንደምትገኝም አክለዋል።

"የአረንጓዴ ልማት አሻራ፣ በምግብ ራስን የመቻል ንቅናቄ፣ የኮሪደር ልማት፣ የታዳሽ ኃይል ማስፋፊያዎች እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን የማረጋጋጥ ተግባራት ብሔራዊ መርኃ-ግብሮች ብቻ ሳይሆኑ ዘላቂ መጻኢ ጊዜን እውን የማድረግ ጥረት አካል ናቸው።"

ትናንት የጀመረው 16ኛው የአፍሪካ የስጋት አቅም አኅጉራዊ ጉባኤ አካል በሆነው የሚንስትሮች ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ጨምሮ የሌሎች አፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0