አንጎላ የኢኮኖሚ ምንጯን ለማስፋት በምታደርገው ጥረት የመጀመሪያውን የወርቅ ማጣሪያ ልትከፍት ነው

ሰብስክራይብ

አንጎላ የኢኮኖሚ ምንጯን ለማስፋት በምታደርገው ጥረት የመጀመሪያውን የወርቅ ማጣሪያ ልትከፍት ነው

እንደ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፤ የማጣሪያ ጣቢያው፦

ቦታ፦ ቪያና፣ ሉአንዳ

ሥራ የሚጀምርበት ጊዜ፦ በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ

አቅም፦ በቀን 20 ኪሎ ግራም ወርቅ

ይህ እርምጃ አፍሪካ ማዕድናትን በሀገር ውስጥ ለማቀነባበር የምታደርገው ሰፋ ያለ ጥረት አካል ሲሆን ይህም ገቢን፣ የሥራ ዕድልን እና የኢኮኖሚ ጥንካሬን ይጨምራል። ለረጅም ጊዜ በነዳጅ እና በአልማዝ ላይ ጥገኛ የነበረችው አንጎላ፤ በዓለም አቀፍ የዋጋ መዋዠቅ በቀላሉ ተጠቂ መሆኗ ለውጡን እጅግ ወሳኝ ያደርግላታል።

ℹ የማዕድን ዘርፉ ለሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 2 በመቶ ገደማ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ የተፈጥሮ ሀብት ማውጫ ኢንዱስትሪው በአጠቃላይ ከ30 በመቶ በላይ ድርሻ ያለው ሲሆን ከ50 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል። አዲሱ ማጣሪያ አንጎላ በአፍሪካ የማዕድን እሴት ሰንሰለት ውስጥ ሚናዋን የማጠናከር ዓላማ አለው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0