ኢትዮጵያ ቻይና መሩን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የአየር ትንበያ ፕሮጀክት ተቀላቀለች

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ቻይና መሩን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የአየር ትንበያ ፕሮጀክት ተቀላቀለች

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እና በፓኪስታን ቀደም ብሎ ሥራ ላይ የዋለውን የ 'MAZU' የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት መነሻ በማድረግ ፈጣን የአየር ሁኔታ ቁጥጥርና የአደጋ ማስጠንቀቂያ አሰጣጥን ያሻሽላል ተብሏል።

ኢትዮጵያም፤ በዚህ የተቀናጀ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ሥርዓት የአጭር እና ረጅም ጊዜ የአየር ሁኔታ ትንበያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅሟን ለማሳደግ አልማለች፡፡


የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባለሙያ ለታ በቀለ፤ “ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የላቁ ቴክኖሎጂዎችን እንድታገኝ፣ ባለሙያዎቿን እንድታሠለጥንና በቅድመ ማስጠንቀቂያ ረገድ ያለባትን ክፍተት እንድትሞላ ይረዳታል” ማለታቸውን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0