ባለፉት አራት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ማግኘታቸው ተገለፀ

ሰብስክራይብ

ባለፉት አራት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ማግኘታቸው ተገለፀ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የሥራ ፈላጊዎችንና አሠሪዎችን በዲጂታል መንገድ በማገናኘት ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።

ሥርዓቱ የሥራ ገበያውን ፍላጎትና አቅርቦት በመረጃ በማገናኘት ዜጎች በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻሉን ሚኒስትር ዴኤታ ሰሎሞን ሶካ ተናግረዋል።

አክለውም በሀገር ውስጥ 45 ሺህ ገደማ ወጣት ምሩቃን በሥርዓቱ አማካኝነት በመደበኛ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እና የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለዜጎች የርቀት እና የፍሪላንስ የሥራ ዕድሎች እንዲሰፉ እገዛ አድርገዋል ማለታቸውን የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0