ኢትዮጵያና ቡሩንዲ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከ12 በኋላ በተካሄደው 2ኛው የኢትዮ-ቡሩንዲ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ፤ ሀገራቱ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና በሰላም ማስከበር ዘርፎች በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና ኤዱዋርድ ኤዚማና የፖለቲካ ግንኙነቱን ወደ ተግባራዊ ጥቅም ለመለወጥ የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶችን አጽድቀዋል።
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ "ስብሰባው የበለጠ ጠንካራ አጋርነት ለመገንባት የሚያስችል ነው” ሲሉ፤ የቡሩንዲው አቻቸው በበኩላቸው የጋራ ጥቅምን መሠረት ባደረጉ የትብብር ዘርፎች ትስስርን ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X