የትራምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የከለላ ፈቃድ ስረዛ በፍርድ ቤት ታገደ

የትራምፕ አስተዳደር
የትራምፕ አስተዳደር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.04.2026
ሰብስክራይብ
የትራምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የከለላ ፈቃድ ስረዛ በፍርድ ቤት ታገደ

በማሳቹሴትስ የሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ጥበቃውን ለማቋረጥ የሞከረው በኮንግረስ የተቀመጠውን አካሄድ ባልተከተለ መልኩ "ከሕግ ውጭ" በመሆኑ እንዲዘገይ ወስኗል።


የፍርድ ቤቱ ዳኛ ብራያን መርፊ "ፕሬዚዳንታዊ ምኞቶች የኤጀንሲዎችን ሕጋዊ ግዴታ አይተኩም" ብለዋል።


የሀገር ውስጥ ደህንነት መሥሪያ ቤት በበኩሉ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንደተሻሻለና ከለላው ሊያበቃ ይገባል ሲል በመከራከር ውሳኔውን "የአክቲቪስት ዳኞች ጣልቃ ገብነት" ሲል ወቅሶታል።

የትራምፕ አስተዳደር በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ተሻሽሏል በማለት በጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ከጥቅምት 10፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሆነውን የከለላ ፈቃድ ከየካቲት 9፣ 2018 ዓ.ም በኋላ እንደሚሰርዝ አስታውቆ ነበር፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0