የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የሙስና ምርመራዎችን በበጎው ይቀበላል - ፓትሪስ ሞትሴፔ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የሙስና ምርመራዎችን በበጎው ይቀበላል - ፓትሪስ ሞትሴፔ

"በካፍ ዙሪያ በመንግሥትም ይሁን በተቋም ደረጃ የሚደረግ የትንኛውንም ዓይነት የሙስና ምርመራ እቀበላለሁ። ሙሉ ትብብርም እናደርጋለን። ልጆቻችን በሕይወት ስኬታማ ለመሆን ሙሰኛ መሆን አለብህ የሚል ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ የለብንም። ሙስናን ልንታገስ አይገባም" ሲሉ የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ተናግረዋል።

ሞትሴፔ በአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ውዝግብ ዙሪያ ከሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ከፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ጋር ተገናኝተው የስምምነት ጥሪ አቅርበዋል። ዛሬ ሐሙስ በተመሳሳይ በሞሮኮ ውይይቶችን ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዝዳንቱ ለሞሮኮ ተዳልቷል የሚሉ ወቀሳዎችንም ውድቅ አድርገዋል። የትኛውም የአፍሪካ ሀገር ከሌላው በተለየ አይስተናገድም፤ ይህ ፈጽሞ ሊከሰት አይችልም ብለዋል።

ሴኔጋል የካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ በጥር 18ቱ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ በተፈጠረው ትርምስ ምክንያት የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነቷን ቀምቶ ለሞሮኮ በመስጠቱ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቃለች። በጨዋታው ሴኔጋል 1 ለ 0 ብታሸንፍም፤ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች የዳኝነት ውሳኔ በመቃወም ለተወሰነ ጊዜ ከሜዳ ወጥተው እንደነበር ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0