አሜሪካ ኃይሌን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች - ኢትዮጵያዊ ምሁር

አሜሪካ
አሜሪካ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.04.2026
ሰብስክራይብ
አሜሪካ ኃይሌን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች - ኢትዮጵያዊ ምሁር

ዋሽንግተን መሪዎችን በመግደል እና ኃይሏን በመጠቀም ኢራንን በአጭር ግዜ ውስጥ አንበረክካለሁ ብላ አስባ ነበር ሲሉ የወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሀመድ አዎል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“...በተቃራኒው ኢራን ድብደባዎቹን ተቋቁማ፤ መከላከሏን ቀጠለች እንዲሁም የጦር ሜዳውን ወደ ባሕረ ሰላጤው፣ ወደ አረቦች እና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች አስፋፍታለች። በዚህም አሜሪካ የበላይነቷን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች” ብለዋል።


እንደ ባለሙያው ማብራሪያ ዩናይትድ ስቴትስ የተሳሳቱ ስሌቶቿን በድጋሚ ለመገምገም የተገደደችው በዚህ ምክንያት ነው፡፡


“ክልሉን አቅልለው ተመልከተውታል። ለሆርሙዝና ሌሎች አካባቢዎች ዝቅተኛ ግምት ሰጥተዋል። ስለዚህ የመጀመሪያ ስሌታቸውን እንዲገመግሙ ተገደዋል።”


በሌላ በኩል ጦርነቱ የአንድ ኃይል የበላይነት መዳከሙ በግልጽ የታየበት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡


“የአሜሪካ የቅርብ አጋሮች እንኳን ትብብር ነፍገዋል። ስፔን፣ ጣሊያን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይ የአየር ሰፈሮቻቸውን ለዩናይትድ ስቴትስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበሩም። ይህ በእውነቱ የአንድ ኃይል የበላይነት መዳከሙን ያሳያል።”


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0