በአውሮፓ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ "አሳሳቢ አዝማሚያ ነው" - ዛካሮቫ

ሰብስክራይብ

በአውሮፓ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ "አሳሳቢ አዝማሚያ ነው" - ዛካሮቫ

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የሰጧቸው ሌሎች ተጨማሪ መግለጫዎች፦

◻ በአውሮፓ ሀገራት ዘንድ እየታየ ያለው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ድጋፍ ንቅናቄ፤ ዓለም አቀፉን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የቁጥጥር ሥርዓት እያዳከመና እየሸረሸረ ይገኛል፡፡

◻ ሞስኮ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በደስታ ትቀበላለች፡፡ ግጭቱ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ ገና ከጅምሩ ስትሟገት ቆያታለች፡፡

◻ እንደ ኢራን ግጭት ያሉ ሰው ሠራሽ ቀውሶች ዳግመኛ እንዳይከሰቱ ለመከላከል አስተማማኝ ዋስትናዎች ያስፈልጋሉ፡፡

◻ በባህሬን ቀርቦ በሞስኮ እና በቤጂንግ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ውድቅ የተደረገው የጸጥታው ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ቢጸድቅ ኖሮ ለዓለም አቀፍ ሕግ አደገኛ ምሳሌ ሊፈጥር ይችል ነበር፡፡

◻ ዩክሬን ለዓለም አቀፍ የመረጃ ደህንነት ዘላቂ ስጋት መሆኗን የጠቀሱት ቃል አቀባይዋ፤ ሀገሪቱ ለሳይበር ወንጀለኞች መሸሸጊያ ሆናለች ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0