የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ቁጥር ወደ 500 ሊያሳድግ መሆኑ ተነገረ
19:09 08.04.2026 (የተሻሻለ: 19:43 08.04.2026)

ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ቁጥር ወደ 500 ሊያሳድግ መሆኑ ተነገረ
ቢሮው በከተማዋ ያለውን የብዙኃን ትራንስፖርት ተደራሽነት ለማሳደግ እና የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን ለማጠናከር በቀጣይ ሦስት ዓመታት የኤሌክትሪክ አውቶቡሶቹን ለመጨመር እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
አሁን ላይ በመዲናው የሚገኙ 100 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች በቀን 120 ሺህ እያጓጓዙ መሆኑንና የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርሻ ከ36 በመቶ ወደ 42 በመቶ ከፍ እንዳደረጉት ተገልጿል፡፡
የአውቶቡሶቹን ቁጥር ከመጨመር ጎን ለጎን ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ዲፖ ግንባታን ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ገልፀዋል።
በሥራ ላይ ያሉት 100ዎቹ አውቶቡሶች በ6 መነሻ እና በ16 መዳረሻዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የክፍያ እና የስምሪት ሥርዓት በመጠቀም አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X