የኢትዮጵያ ምርቶች በትልቁ የሩሲያ መገበያያ መድረክ መቅረብ ጀመሩ

ዋይልድቤሪስ
ዋይልድቤሪስ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.04.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ምርቶች በትልቁ የሩሲያ መገበያያ መድረክ መቅረብ ጀመሩ


"ዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ምርቶችን ሩሲያ ውስጥ መሸጥ መጀመሩን ያበስራል። በመድረኩ ላይ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች እና መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ ማስጌጫዎች እንዲሁም የተፈጥሮ የመዋቢያ ምርቶች ያሉ የኢትዮጵያ አምራቾች የምርት ውጤቶች ይቀርባሉ" ሲሉ የመገበያያ መድረኩ መስራች ታቲያና ኪም በኢኖቬቲቭ ኢ-ኮሜርስ እና ሚዲያ ቴክኖሎጂዎች ኮንፈረንስ ላይ አስታውቀዋል።


ታቲያና ኪም በንግግራቸው፤ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ባለው የምስራቅ አፍሪካ ገበያ፤ ከሩሲያ ጋር የሚቀራረብ ወጣት የሕዝብ ቁጥር ያላት በመሆኑ እና መንግሥት ለዲጂታላይዜሽን በሚሰጠው ጠንካራ ድጋፍ ምክንያት ከፍተኛ የኢ-ኮሜርስ አቅም አላት ብለዋል።

ዋይልድቤሪስ ገዢዎችንም ሆነ ሻጮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎቹን በማጋራት፤ ለአፍሪካ የኢ-ኮሜርስ እድገት ቁልፍ የቴክኖሎጂ አጋር ለመሆን ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር የተፈጠረውን አጋርነት ተከትሎ ኢትዮጵያ የዋይልድቤሪስ 11ኛው የገበያ መዳረሻ ሆናለች።

▫ በቀጣይ ምዕራፍ መድረኩ ለኢትዮጵያውያን ሸማቾች ክፍት የሚሆን ሲሆን ይህም ሩሲያውያን ሻጮች ተስፋ ሰጪ የሆነውን አዲሱን የኢትዮጵያ ገበያ እንዲቀላቀሉ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0